ሳይደፈርስ አይጠራም ሳይጨልም አይነጋም

ሰላዮችን ራሳቸው በራሳቸው በመጋለጣቸው የነፃነት ትግሉን የበለጠ ይጠነክራል ይጠራል እንጂ ፍፁም አይቆምም::

1-G5

ከዘርኣይ ደረስ ደበሳይ

ሞላ አስገዶም የወያኔ ተላላኪና ሰላይ ሆኖ ትግሉን የማኰላሸት ስራ የሚሰራ ብቻ ሳይሆን ከውጭ ሀገር ደላሎች ጋር በመመሳጠር የኩላሊት ነጋዴም በመሆን የትግራይ ለጋ ወጣቶችን እየመለመለ ወደ ዓረብ ሀገሮችን በመሸጥ በትግራይ ህዝብ ደም ሲነግድ የነበረ ደለላም ጭምር እንደነበር የታመኑ ምንጮች ይገልፃሉ:: ዛሬ በህፃናቱ ደም የሰበሰበውን በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ይዞ ተመልሶ ወደ ኢትዮያ ቢገባ የሚያስገርም አይሆንም:: የሚያስገርመው ግን በአንድ በኩል ከወያኔ መንግስት የሚያገኘው ገንዘብ በሌላ በኩል ደግሞ ለአንድ ወጣት ትግራዋይ ከሶስት እስከ አምስት ሽሕ ዶላር ወደ ውጭ እየቸበቸበ የሚያገኘው ገቢ እንዲሁም የነፃነት ታጋይ ነኝ በሚል ሽፋኝ ከኤርትራ መንግስትና ከሌሎች ታጋይ ሀይሎች ይደረግለት የነበረውን የገንዘብ ድጋፍ ተደማምሮ ሲታይ ይህን ሁሉ ቴክኒክ ለማቀነባበር የተጠቀመበት ስልትና ስትራተጂ አስገራሚ ነው:: የሚያሳዝነው ደግሞ በማያውቁት ጉዳይ ላይ የእሳት ራት ሆነው የቀሩ የትግራይ ወጣቶችን ነው:: ትግራይ እንደነ አሉላ አባ ነጋና ሐየሎም አርአያ የመሳሰሉትን የነፃነት አንበሶች እንዳልወለደች ሁሉ ዛሬ የጥቂት ደላሎችና ካሃዲዎች መፈልፊያና መናሃሪያ በመሆን ” የሰው ልጅ እንደ ከብት በቁሙ የሚሸጥባት የሲኦል ምድር ሆና ሳያት እጅግም ያሳዝነኛል:: ይዘገንነኛልም::

ታሪክ ራሱ ይደግማል እንዲሉ ቀደም ሲል ወያኔ በትጥቅ ትግሉ ዘመን ይጠቀምበት የነበረውን በትግራይ ህዝብ ደም ንግድ ዛሬም በደምሒት በነ ሞላ አስገዶም መደገሙ ሌላው በህዝባችን ላይ የተፈፀመ ጥቁር ታሪክ ነው:: (በዚሁ የሞላ አስገዶም የኩላሊትና የወጣቶች ንግድ በሚመለከት ሌላ ጊዜ በሰፊው ለማቅረብ እሞክራለሁ) ለዛሬው ግን ወደ ተነሳሁበት ርእስ ጉዳይ ልመለስ::

ሰሞኑን የህወሓት ሰላይ በመሆን በትግራይ ለጋ ወጣቶች ላይ የፓለቲካ ቁማር ሲጫወት የቆየው ሞላ አስገዶም የተወሰኑ የደምሒት አባላት ይዞ ከትግል ሜዳ አፈንግጦ ኰበለለ የሚል ዜና ግራና ቀኙን ሲናፈስና የተለያዩ ሰዎች በዘፈቀደ የየራሳቸውን ትርጉም በመስጠት ሲናገሩና ሲፅፉ ሰንብቷል:: ወሬው አሁንም በሰፊው በመዛመት ላይ ይገኛል:: የህወሓት መንግስትም በጉዳይ ላይ ቀጥተኛ እጅ እንዳለበት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል:: አዎ “መቆየት ደጉ ብዙ አሳየን” እንደ ተባለው ሁሉ ዕድሜ የሰጠው ሰዉ ገና ብዙ አዳዲስ የትግል ሁኔታዎችንንና ክስተቶችን ያያል::

ቀደም ሲል ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በመሆን ወደ ኤርትራ ወደ ትግል ሜዳ ገባ የሚል ዜና እንደሰማሁ በአእምሮዬ ውስጥ “አለ ነገር” የሚል ስሜት ተቀላቀለብኝ:: ይህን ያልኩበት ምክንያትም በኢትዮያ አቆጣጠር በ97 በተደረገው የምርጫ ቅስቀሳና የምረጡኝ ክርክር የዶክተር ብርሃኑ ተሳትፎ ምን ያህል የኢትዮያ የፓለቲካ ድባብ እንደቀየረውና የመለስ ዜናዊ መንግስትን ከስረ መሰረቱ እንዴት እንዳናጋው ዓቅሙም ! እውቀቱም ” የፓለቲካ ብስለቱም በተግባር ስላየሁት እጅግ ከማደንቃቸው የኢትዮያ የቀውጥ ቀን ልጆች አንዱ ነው:: ዛሬ እንደገና እነ ዶክተር ብርሃኑ ይህን ሁሉ ፈተና አልፈው ወደ ትግል ሜዳው እንዲቀላቀሉ ያደረጋቸው በስተጀርባቸው ያለው ሚስጢራዊ ሀይል ምንድን ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ የአላማ ፅናት ” የሀገርና የወገን ፍቅር ” የነፃነትና የፍትሕ ጥማት” የአባቶቻችን ያልገዛም ባይነት ወኔና የሰማእታቱን አደራ ናቸው ብዬ አምናለሁ:: በአጠቃላይ “ነፃነት ወይም ሞት” የሚል የአባቶቻችን የቃል ኪዳን አሻራ አንግበው ወደ ላቀ የትግል ሜዳ መሄዳቸው ስሰማ ምናልባት የሚከተሉትን የትግል ሁኔታዎች መልክ ሊይዙና መልስ ሊያገኙ ይችላሉ የሚል ብሩህ ተስፋና እምነት አድሮብኛል::

  1. የሀገራችን ምስቅልቅል የፓለቲካ ገፀ ባህርይ ፈር የሚያስይዝ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃ ቀንድ ታጋዮችን የሚያስተሳስር ብሩህ የትግል ጎዳና ይፈነጥቃል ” ሚሊዮኖችን ከእንቅልፍ ይቀሰቅሳል ” እንክርዳዱን ከምርቱ አንጓልሎ አንጓልሎ ይለያል ” መስመሩን አስተካክሎ ፋኖ ወደ ሀገሩ ያመራል የሚል ወለል ብሎ እንዲታየኝ አድርጎኛል::
  2. እስካሁን ድረስ በትጥቅ ትግሉ ሜዳ አሉት የሚባሉትን የፓለቲካ ድርጅቶችና የተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦች የነፃነት ታጋዮች ነን የሚሉ አንዳንድ ሀይሎች ኤርትራን መታገያ ሳይሆን መጠሊያ ! ፓለቲካን ማስተባበሪያና አንድነት መፈጠሪያ ሳይሆን መተዳደሪያ አድርገውት “ላም አለችኝ በሰማይ ወተትዋን ግን አላይ” ሆነው ቆይቷል:: አሁን ግን እነዶክተር ብርሃኑና ሌሎች ታጋዮች በአካል ፊት ለፊት ተቀራርበው ወደ አንድነትና ውሕደት የሚያመራ ቀጥተኛ ውይይት መጀመራቸው ትግሉን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እርምጃ ብቻ ሳይሆን ራሱን የቻለ አዲስ ውስጣዊ የጥራት ትግል እየተፋፋመ መሆኑን በነሞላ አስገደም በደምሒት ላይ እየታየ ያለው ሁኔታ ያመላክታል:: የነ ዶክተር ብርሃኑ ኤርትራ መሄድ በወያኔና በነሞላ አስገደም ያለው እኩይ ተግባር እንዲጋለጥ ማድረጉ ራሱ ለትግሉ ጎራ ውድቀት ሳይሆን ትልቅ ድል ነው ብዬ አምናለሁ:: ሳይደፈርስ አይጠራምና ነው::
  3. በኤርትራና በኢትዮያ መካከል ያለው የተዘበራረቀና የደፈረሰ ጉዳይ የኢትዮያ ህዝብ ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ” አንዳንድ ወሬ አቀባባዮች እንደፈለጉ የሚመነዙሩበትና የሚያደናግሩበት ስለሆነ ለህዝቡ ሕቡእ ወይም ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል:: አሁን ግን ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም በሁለቱም ህዝቦች መካከል ሊኖር የሚገባው ሀቀኛና ወንድማዊ ግንኙነት እንደ ድልድይ ሆኖ ሊያገለግል የሚችል ጠንካራ ሀይል ሊፈጠር ይችላል የሚል እምነት አለኝ:: እንደ በፊቱ ሁለቱን ህዝቦች እርስ በርስ እያናከሱና የፓለቲካ መሳሪያ እያደረጉ ከመኖር ይልቅ ተደጋግፈው የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ የሚፈቱበትን ሁኔታ የሚያመቻች ሀይል ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ::
  4. በቅርቡ በዶክተር ብርሃኑ እንደተገለፀው በታጋይ ሀይሎች መካከል መተባበርና ወደ አንድ ሀገራዊ ራዕይ የሚያመራ የትግል ፈር መያዝ ማለት ነገ በተጨባጭ በተግባር ሊታይ የሚችል ” የኢትዮያ ህዝብ ጠላቶችን ዕድሜ የሚያሳጥር ” በአንፃሩ ደግሞ የኢትዮያ ህዝብን እንደ አንድ ቤተሰብ የሚያስተቃቅፍና የሚያሰባስብ ተስፋ ሰጪ ሀይል ሊሆን ይችላል የሚል ብሩህ ተስፋ አለኝ:: እየከሰመ ! እየሻገተና እየተፈረካከሰ በመሄድ ላይ የሚገኘው አረሜኔው የወያኔ ስርዓት የነ ዶክተር ብርሃኑ ወደ ትግል ሜዳው መቀላቀል ምን ያህል እንዳስደነገጠውና እንዳስጨነቀው ሰሞኑን ራሱ ካወጣው ይፋዊ መግለጫ መረዳት ይቻላል::

ሞላ አስገደምና ግብረ አበሮቹ ከመቅፅበት ወደ አሳዛኝና አስገራሚ የጥፋት ድራማ እንዲገቡ ያደረጋቸው ምንድን ነው?

ሰሞኑን ተፈጠረ ስለተባለው የደምሒት መሪዎች ከትግል ሜዳው መሸሽና መኰብለል በሚመለከት የተለያዩ ስሜቶች ! ሀሳቦችና አስተያየቶች ሲሰጥ ሰንብቷል:: በተለይም የመንግስት ደጋፊዎችና ካድሬዎች ልክ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በመንግስት ቁጥጥር ስር መግባቱ እንደ ትልቅ የትጥቅ ትግሉ ውድቀት አድርገው ሲያወሩ እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ለራሳቸው ተደናግረው ሌላውን ሲያደናግሩ ታይቷል:: ሌሎቹም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የየራሳቸው የመሰላቸውን ሀሳብ ሲያስተጋቡ ይታያሉ::

በኔ እምነት በደምሒት ውስጥ የተፈጠረ ሁኔታ ከላይ ላዩ ሲታይ መሆን ያልነበረበት መጥፎ ዜና ቢሆንም በሌላ መልኩ ግን ከላይ ከ1 እስከ 4 የተጠቀሱትን ነጥቦች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ቅደመ ሁኔታዎችን መስራት እንደተጀመሩ የሚያመላክት ነው:: ምክንያቱም

  • ወደ ፈታኝ የትግል መስመር በተሻገርክና ወደ አዲስ የትግል ምዕራፍ በገባህ ቁጥር መንጠባጠቡና በሀሳብ መለያየቱ የግድ ይላል:: የአላማ ፅናት! የፓለቲካ ብስለት ! ውስብስብ የትግል ስልትና ስትራተጂ በብቃት የመመራትና ያለመምራት የሚለካውም እንደአሁኑ ፈታኝ የትግል መድረክ ሲመጣ ነው:: ምርቱንና እንክርዳዱን የሚለው በዘሁ ነው::
  • ሗላቀር የፓለቲካ ባህል ዋናው የችግሮቻችን መንሲኤ አንዱ ነው:: ልዩነት ይዞ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተቻችሎ አብሮ የመስራት ባህል ያልተለመደ ዱብ ዕዳ አድርጎ የመመልከት ችግር በብዙ ፓለቲከኞች የሚታይ ድክመት ነው:: በኤርትራ ያሉት የፓለቲካ ድርጅቶችም በመካከላቸው ሀገርንና ህዝብን ማእከል ያደረገ ” በመተማመንና በንቃት ላይ የተመሰረተ ነፃ ግንኙነት አዳብረው ቆይቷል ብሎ መናገር ያስቸግራል:: ዛሬ እስከ ውህደት የሚደርስ ነፃ ውይይት ሲጀመር ግን ስንቱን ሊያስደነግጥና ሊያስበረግግ እንደሚችል መገመቱ አያስቸግርም:: ይኽውና በደምሒት የተፈጠረው አንዱ አብነት ነው:: አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል እንዲሉ ሞላ አስገደሞ ሲመታ የአዲስ አበባ መንግስት ተናጋ::
  • ሶስተኛው ችግር ለግል ጥቅምና ዝና ሲባል ሀገርንና ህዝብን መሸጥ የተለመደ ተግባር ሆኗል:: ሞላ አስገዶም የህወሓት የውስጥ ሰላይ በመሆን ትግሉን ብቻ አይደለም ለመጉዳት የሞኮረው:: ከህወሓት ጋር በመመሳጠር የትግራይ ለጋ ወጣቶችን በነፃ አውጪነት ስም እየመለመለ ወደ ጦርነት በማሰለፍና ወደ ውጭ ሀገር በመሸጥ በማያውቁት ጉዳይ ላይ ሰለባ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ በመጨረሻ ወጣቶቹን በታትኖ የራሱን ህይወት ብቻ ለማዳን ሲል በሜዳ ላይ ጥሏቸው የፈረጠጠ መሆኑን ነው::

በደምሒት ላይ የታየው ቀውስ ለሌሎች የኢትዮያ ፓለቲካ ድርጅቶች ያለው እንድምታና መልእክት ምንድን ነው?

የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት የደምሒትን እንቅስቃሴ በስለላ መረቡ አማካይነት በቅርብ ይከታተለው እንደነበርና ሞላ አስገደምና ግብረ አበሮቹም ከህወሓት በሚሰጣቸው መርሃ ግብር መሰረት የሌሎቹን የፓለቲካ ደርጅቶች እንቅስቃሴ

Source: Zehabesha